am_tn/isa/07/23.md

1.9 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ የአሦር ሰራዊት የእስራኤልን ምድር የሚያጠቃው መቼ እንደሆነ መግለጹን ቀጥሏል፡፡

አንድ ሺህ የወይን ተክል… ኩርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል

1,000 የወይን ተክል›› ያም ማለት ኢሳይያስ በጻፈበት ጊዜ አንዳንዶቹ 1000 የወይን ተክል የያዙ የወይን እርሻ ቦታዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የወይን እርሻዎች ግን፣ ኩርንችትና እሾኽ እንደሚሞላባቸው ይናገራል፡፡

ሺህ ሰቅል ብር

1,000 ሰቅል ብር›› ሰቅል የ4 ቀን ደመወዝ የሚሆን የብር ሳንቲም ነው አማራጭ ትርጒም፣ 1,000 የብር ሰቅል››

ኩርንችትና እሾህ

‹‹ኩርንችት›› እና፣ ‹‹እሾኽ›› ሁለቱም የሚያመለክቱት ጥቅም የሌላቸው ተክሎችን ነው፡፡ ሁለቱንም ቃሎች መተርጐም አስፈላጊ አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእሾህ ቁጥቋጦ›› ወይም፣ ‹‹የኩርንችት ቁጥቋጦ››

ምድሩ ሁሉ ኩርንችትና እሾኽ ስለሚሆን

አዳኞቹ ወደዚህ ቦታ የሚመጡበትን ምክንያት ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚያ ቦታ ኩርንችትና እሾኽ እንዲሁም የዱር አራዊት እንጂ፣ ሌላ ምንም ስለማይኖር››

ከዚያ በፊት በመቆፈሪያ ተቆፍረው ወደ ነበሩት ኮረብታዎች አይሄዱም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ከዚያ በፊት እህል ለመዝራት ዝግጁ ወደ ነበሩት ቦታዎች አይሄዱም››