am_tn/isa/07/20.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ የአሦር ሰራዊት እስራኤልን የሚወርረው መቼ እንደሆነ መግለጹን ቀጥሏል፡፡

እግዚአብሔር ከወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ ማለትም በአሦር ንጉሥ ይላጫል

‹‹ምላጭ›› የአሦር ንጉሥና ሰራዊቱን ያመለክታል፤ ንጉሡ የያህዌን ሥራ የሚሠራና ለዚያም ከያህዌ ገንዘብ እንደሚቀበል ሰው እንደሆነ ያህዌ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እናንተን እንዲላጭ የአሦርን ንጉሥ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ይጠራዋል››

በተከራየው

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በገዛው››

የራስና የእግር ጠጉራችሁን… ጢማችሁን

የአንድን ሰው አናት መላጨት መጥፎ ነው፤ ‹‹የእግርን ጠጉር›› መላጨት የባሰ መጥፎ ነው፤ ጢምን መላጨት ደግሞ ከሁሉ የባሰ መጥፎ ነው፡፡

የራስና የእግር ጠጉራችሁን… ጢማችሁን

እግዚአብሔር የሚላጨው የማንን ራስ ጠጉርና ጢም እንደሆነ ኢሳይያስ አይናገርም፤ አካዝና አንባቢዎቹ ግን ይህ የሚያመለክተው ስለ ሰው መሆኑንና ያ ደግሞ በይሁዳ ምድር የሚኖረውን ሕዝብ ሊያመለክት እንደሚችል ይረዳሉ፡፡

ራስ

‹‹ራስ›› እዚያ ላይ የሚበቅል ጠጉርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የራስ ጠጉር››

የእግር ጠጉር

ይህም ማለት 1) የሰውነት ታችኛው አካል ላይ የሚበቅል ጠጉርን በጨዋነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ሐረግ ሊሆን ይችላል፤ ወይም 2) እግር ላይ የሚበቀለውን ጠጉር የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡

እንዲሁም… ይላጫል

‹‹እንዲሁም ምላጩ… ይላጫል›› ቋንቋህ፣ ‹‹የሚላጭ ሰው›› እንዲኖር የሚጠይቅ ከሆነ፣ ‹‹እግዚአብሔር ይላጨዋል›› ማለት ትችላለህ፡፡

ከሚሰጡት የተትረፈረፈ ወተት የተነሣ

‹‹የተትረፈረፈ›› የሚለውን በሌላ መልኩ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም ብዙ ወተት ከመስጠታቸው የተነሣ››