am_tn/isa/07/16.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ እግዚአብሔር ለዳዊት ቤት ስለሚሰጠው ምልክት መግለጹን ቀጥሏል፡፡

ክፉውን መተውና መልካሙ መምረጥ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ክፉው›› እና፣ ‹‹መልካሙ›› በአጠቃላይ ክፉና መልካም ነገሮችን ያመለክታል፡፡ ኢሳይያስ 7፥15 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክፉ ነገሮችን በመተው መልካም ነገሮች ለማድረግ መምረጥ››

የሚያስደነግጡህ

‹‹የፈራሃቸው›› እዚህ ላይ፣ ‹‹አንተ›› ነጠላ ቁጥር ሲሆን፣ አካዝን ያመለክታል፡፡

ሕዝብህ

ይህ የሚያመለክተው የይሁዳን ሕዝብ ነው፡፡

ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን

እዚህ ላይ፣ ‹‹ኤፍሬም›› እና፣ ‹‹ይሁዳ›› በዚያ አካባቢ የሚኖረውን ሕዝብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከይሁዳ ሕዝብ የተለየው የኤፍሬም ሕዝብ››