am_tn/isa/07/13.md

2.6 KiB
Raw Permalink Blame History

የዳዊት ቤት

‹‹ቤት›› ማለት፣ ቤት ውስጥ የሚኖር ቤተ ሰብ ማለት ነው፡፡ ኢሳይያስ 7፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ንጉሥ አካዝና አማካሪዎችህ››

የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላኬን ትዕግሥት ትፈታተናላችሁን?

ይህ አጽንዖት የሚሰጠው ሕዝቡ ታላቅ ኀጢአት ማድረጋቸውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰውን ትዕግሥት ትፈታተናላችሁ! አሁን ደግሞ የአምላኬን ትዕግሥት ትፈታተናላችሁ!

ወጣት ሴት ትፀንሳለች

አንዳንድ የጥንት ቅጂዎችና፣ አንዳንድ የዘመኑ ቅጂዎች፣ ‹‹ድንግል ትፀንሳለች›› በማለት ተርጒመዋል፤ ሌሎች፣ ‹‹ወጣት ሴት ትፀንሳለች›› የሚል ትርጒም ይዘዋል፡፡

ስሙንም አማኑኤል

ተርጓሚዎች፣ ‹‹አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው›› የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ይችላሉ፡፡

ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ሲችል ቅቤና ማር ይበላል

ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ሕፃኑ አድጐ ቅቤና ማር ለመብላት ሲደርስ፣ ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ይችላል›› ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ሕፃኑ ክፉ ከሆነው ይልቅ፣ መልካሙን የሚያውቀው ገና በሕፃንነቱ እንደሆነ ይህ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ ወይም 2) ሕፃኑ አድጐ ክፉውን ትቶ፣ መልካሙን ሲመርጥ ቅቤና ማር ይበላል›› አይሁድ አንድ ሕፃን መልካሙን ለማድረግ ኀላፊነት የሚኖረው 12 ዓመት ሲሞላው እንደሆነ ያምናሉ፡፡ አብዛኞቹ እስራኤላውያን ስለሚገደሉ ወይም በምርኮ ስለሚወሰዱ በዐሥራ ሁለት ዓመት ውስጥ ሕዝቡ ብዙ ቅቤና ማር እንደሚበሉ ይህ አጽንዖት ይሰጣል፡፡

ቅቤ

ሰዎች ከወተት የሚያወጡት ጠጣሩ ክፍል

ክፉውን መተው መልካሙን መምረጥ

እዘህ ላይ፣ ‹‹ክፉው›› እና፣ ‹‹መልካሙ›› በአጠቃላይ ክፉና መልካም ነገሮችን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክፉ ነገሮችን በመተው መልካም ነገሮችን ለማድረግ መምረጥ››