am_tn/isa/07/03.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ሌሎች ላይ የደረሰው እርሱ ላይ እንደ ደረሰ ይናገራል፡፡

ሸአር ያሹብ

ተርጓሚዎቹ፣ ‹‹ሸአር፣ ያሹብ፣ ‹ትሩፋኑ ይመለሳሉ› ማለት ነው የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ይችላሉ፡፡ ትርጒሙ ለአካዝ ተስፋ ይሰጠዋል፡፡

የላይኛው የኩሬ መስኖ ጫፍ

‹‹ውሃው በቦይ አልፎ ወደ ላይኛው ኩሬ የሚገባበት››

መስኖ

ውሃ የሚያልፍበት ሰው ሠራሽ መተላለፊያ

መንገድ

ቋንቋህ ዝቅ ያለውን ቦታ በመሙላት፣ ከፍ ያለውን በመደልደል የተመቸ እንዲሆን ሰዎች የሚሠሩትን መንገድ ወይም ጐዳና የሚያመለክት ቃል ካለው እዚህ ላይ መጠቀም ትችላለህ፡፡

የልብስ አጣቢው መስክ

ይህ ማለት፣ 1) ሰዎች ያንን መስክ የሚጠሩበት የተለመደ ስም ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም 2) ሰዎች ያንን መስክ፣ ‹‹የልብስ አጣቢው መስክ›› የሚል ስም ስለ ሰጡት ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ‹‹ሰዎች ልብስ የሚያጥቡበት ቦታ›› ወይም፣ ‹‹ሴቶች ልብስ የሚያጥቡበት ቦታ›› ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

የልብስ አጣቢው መስክ

ልብስ አጣቢው፣ 1) ከበጐች የተሸለተውን ጠጉር የሚያጥብ ሰው፤ ‹‹የበግ ጠጉር አጣቢው›› ወይም 2) የቆሸሸ ልብስ የምታጥብ ሴት›› ‹‹የልብስ አጣቢዋ መስክ››

ንገሩት

‹‹ለአካዝ ንገሩት››

አትፍራ፤ በእነዚህ ከእሳት ተርፈው በሚጤሱት በሁለቱ የእንጨት ጉማጆች በሶርያና በንጉሥዋ በረአሶን እንዲሁም በሮሜልዩ ልጅ ቁጣ አትሸበር

እግዚአብሔር ረኦሶንና ፋቁሔን ነድዶ እሳቱ ከወጣለት፣ አሁን ግን ጭስ ብቻ ከተረፈው የእንጨት ጉማጅ ጋር ያመሳስላቸዋል፡፡ ለይሁዳ ይህን ያህል የሚያሰጉ እንዳይደሉ እግዚአብሔር አስረግጦ ይናገራል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ረአሶንና ፋቁሔን አትፍራ፤ የእነርሱ ቁጣ እሳቱ ወጥቶ ጭስ ብቻ እንደ ቀረው የእንጨት ጉማጆች ናቸው፡፡

አትፍራ ወይም አትሸበር

‹‹አትፍራ›› እና፣ ‹‹አትሸበር›› የተሰኙት ቃሎች ትርጒም ተመሳሳይ ስለሆነ በአንድ ቃል መተርጐም ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አትፍራቸው››