am_tn/isa/06/11.md

857 B

ከተሞች እስኪፈራርሱ፣ ቤቶችም የሚኖርባቸው እስኪያጡ

‹‹ማንም እንዳኖርባቸው ከተሞችና ቤቶች እስኪወድሙ ድረስ››

ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ

‹‹ባድማ›› መሆን አስከፊ ደረጃ ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምድሪቱ ጠፍ ምድረ በዳ እስክትሆን››

ያህዌ ሕዝቡን ወደ ሩቅ እስከሚሰድና የምድሪቱ ባዶነት ከባድ እስኪሆን

እዚህ ላይ ያህዌ ስለ ራሱ በሦስተኛ ሰው ደረጃ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ያህዌ ሕዝቡን ከምድራቸው ወደ ሩቅ አገር እስከምሰድና እዚያ ማንም እስከማይቀር ድረስ››