am_tn/isa/06/10.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ለሕዝቡ እንዲሰብክ ሲልከው ምን ማለት እንዳለበት ያህዌ ለኢሳይያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን

‹‹ልብ›› የሚወክለው የሰውን አእምሮ ነው፡፡ በደንብ የማይሰማና መረዳት የማይችል ሰው ልቡ የደነደነ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ ሕዝብ መረዳት እንዳይችል አድርግ›› ወይም፣ ‹‹የዚህን ሕዝብ አእምሮ ደነዝ አድርግ››

የዚህን ሕዝብ ልብ

‹‹ልብ›› እና፣ ‹‹የዚህ›› የሚሉትን ቃሎች በብዙ ቁጥር መተርጐም የበለጠ አግባብነት ይኖረዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእነዚህን ሰዎች ልቦች››

ልብ… አደንድን

የተሰጠው ትእዛዝ የኢሳይያስን መልእክት እንዳያስተውሉ ለማድረግ፣ ያህዌ እያደረገ ላለው የበለጠ ደንዳኖች እንዲሆኑ ያህዌ የሚጠቀምበት መሆኑ ነው፡፡

ጆሮአቸውን ድፈን፤ ዐይኖቻቸውንም አሳውር

‹‹እንዳይሰሙ አድርገው፤ እንዳያዩ አድርገው›› ኢሳይያስ ሰዎች የያህዌን መልእከት እንዳያስተውሉ ማድረጉ ወይም እያደረገ ያለው ደንቆሮና ዕውሮች እያደረጋቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በዐይናቸው ዐይተው፤ በጆሮአቸውም ሰምተው

x