am_tn/isa/06/08.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ስለ ራእዩ መግለጹን ቀጥሏል

የጌታም ድምፅ እንዲህ አለ

‹‹ድምፁ›› ጌታ ራሱን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ እንዲህ አለ››

ማንን እልካለሁ?

ይህ የሚያመለክተው የእርሱን መልእክት ለእስራኤል ሕዝብ እንዲናገር ያህዌ አንድ ሰው እንደሚልክ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለሕዝቤ መልእክተኛ እንዲሆን ማንን እልካለሁ››

ማንስ ይሄድልናል?

‹‹እኛ›› የሚለው የሚያመለክተው ያህዌንና እርሱ እየተናገራቸው ያለውን የሰማይ መማክርት ነው፡፡

ይህ ሕዝብ

‹‹የእስራኤል ሕዝብ››

ይሰማሉ፤ ግን አያስተውሉም፤ ያያሉ ግን ልብ አይሉም

ይህም ማለት፣ 1) ‹‹አያስተውሉም›› እና፣ ‹‹ልብ አይሉም›› የሚሉት ያህዌ የሚያደርገውን ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ትሰማላችሁ ግን ያህዌ እንድታስተውሉ አያደርጋችሁም፤ በጥንቃቄ ታያላችሁ ግን ያህዌ ልብ እንድትሉ አያደርጋችሁም›› ወይም 2) ‹‹መስማት›› እና፣ ‹‹ማየት›› የተሰኙት ሐረጐች ‹‹እንዲህ ቢሆን›› የሚል ሐሳብ ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብትሰሙ እንኳ አታስተውሉም፤ በጥንቃቄ ብታዩ እንኳ ልብ አትሉም››

ይሰማሉ ግን አያስተውሉም፤ ያያሉ ግን ልብ አይሉም

በውስጠ ታዋቂነት ያለውን መረጃ መግለጽ ይቻላል፡፡ ‹‹የያህዌን መልእክት ይሰማሉ፣ ግን ምን ማለት እንደ ሆነ አያስተውሉም፤ ያህዌ እያደረገ ያለውን ያያሉ፤ ግን ምን እንደሆነ አይገነዘቡም››