am_tn/isa/06/06.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ስለ ራእዩ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ሱራፌል

እነዚህ ፍጥረታት እሳት፣ የእሳት ነበልባልና እባብ መሰል ሁኔታ ሳይኖራቸው አልቀረም፡፡ ‹‹ሱራፌል›› ምን ማለት እንደ ሆነ በትክክል ስለማይታወቅ፣ ‹‹ፍጡሮች›› ወይም፣ ‹‹ሕያው ነገሮች›› ወይም፣ ‹‹ኅላዌ›› በማለት መተርጐም ትችላለህ፡፡ ወይም ይህን ቃል ወስደህ ቋንቋህ ውስጥ ልትጠቀምበት ትችላለህ፡፡ ኢሳይያስ 6፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

ጉጠት

ነገሮችን ለመያዝ የሚረዳ መሣሪያ

በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኀጢአትህም ተሰርዮልሃል

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ የሚናገሩት ስለ ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ በደልህን አስወግዷል፤ ኀጢአትህንም ይቅር ብሎልሃል››

በደልህ ተወግዶአል

ያህዌ አንድን ሰው ከእንግዲህ እንደ በደለኛ እንደማይቆጥረው ለማሳየት፣ ‹‹በደል›› አንድ ሰው ከሌላው የሚወስደው ነገር እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡