am_tn/isa/06/03.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ስለ ራእዩ መናገሩን ቀጥሏል

እርስ በርሳቸውም በመቀባበል እንዲህ ይሉ ነበር

‹‹ሱራፌል በመቀባበል እንዲህ ይሉ ነበር›› ወይም፣ ‹‹ባለ ክንፍ ፍጥረቶቹ አንዱ ለሌላው እንዲህ ይል ነበር››

ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ጌታ እግዚአብሔር

‹‹ቅዱስ›› የሚለው ቃል ሦስት ጊዜ መደጋገሙ እግዚአብሔር ፍጹም ቅዱስ እንደሆኑ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ ያህዌ ከሁሉም በላይ ቅዱስ ነው፡፡ ወይም፣ ‹‹ጌታ ያህዌ ፍጹም ቅዱስ ነው››

ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች

ይህ ምድር መያዣ እንደሆነች፣ ክብር ደግሞ መያዣውን የሚሞላ ነገር እንደ ሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በምድር ያለ ማንኛውም ነገር የእግዚአብሔር ክብር ማስረጃ ነው››