am_tn/isa/06/01.md

2.2 KiB

ከፍ ባለና በከበረ

‹‹ከፍ ያለ››እና፣ ‹‹የከበረ›› የተሰኙት ቃሎች ዙፋኑ በጣም ከፍ ያለና በዙሪያው ካሉት ሁሉ በላይ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ የዙፋኑ ከፍታ ጌታ ምን ያህል ታላቅና ኀያል መሆኑን ያመለክታል፡፡

ቤተ መቅደሱን ሞላው

‹‹ቦታውን ሞላው››እዚህ ላይ ቤተ መቅደስ ለማለት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል ብዙውን ጊዜ ቤተ መንግሥትን ነው የሚያመለክተው፡፡

ከበላዩም ሱራፌል ነበሩ

‹‹ሱራፌል›› የሚለው ቃል፣ ሱራፍ የሚለው ብዙ ቁጥር ነው፡፡ ይህም ማለት ጌታ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ሱራፌልም ለማገልገል ዝግጁ ሆነው ጌታ አጠገብ ቆመው ነበር ወይም እየበረሩ ነበር ማለት ነው፡፡

ሱራፌል

ይህ ቃል እነዚህ ፍጡራን የእሳት ነበልባል ወይም እባብ የሚመስል ሁኔታ ሳይኖራቸው እንዳልቀረ ያመለክታል፡፡ ‹‹ሱራፌል›› ምን ማለት እንደ ሆነ በትክክል ስለማይታወቅ ‹‹ባለ ክንፍ ፍጥረቶች›› ወይም፣ ‹‹ክንፋም ሕያው ፍጥረቶች›› በማለት መተርጐም ትችላለህ፡፡ ወይም ቃሉን ወስደህ በቋንቋህ ልትጠቀምበት ትችላለህ፡፡

እያንዳንዱ ስድስት ክንፎች ነበሩት

‹‹እያንዳንዱ ሱራፍ ስድስት ክንፎች ነበሩት›› ወይም፣ ‹‹እያንዳንዱ ፍጡር ስድስት ክንፎች ነበሩት››

በሁለቱ ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱ እግራቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ይበሩ ነበር

‹‹ክንፍ›› እና፣ ‹‹ሱራፍ›› የተሰኙት ቃሎች ውስጠ ታዋቂ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እያንዳንዱ ሱራፍ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፤ በሁለቱ ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፤ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር››