am_tn/isa/05/29.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ይሁዳን ስለሚያጠቃው ሰራዊት መግለጹን ቀጥሏል፡፡

ሠረገሎቹ እንደ አንበሳ ያገሳሉ፤ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣሉ፡፡

እነዚህ ሐረጐች በመሠረቱ የሚናገሩት ስለ አንድ ነገር ነው፡፡ ድምፃቸው የይሁዳን ሕዝብ በጣም እንደሚያስፈራ ለማመልከት ኢሳይያስ የጠላትን ሰራዊት ከአንበሳ ጋር ያመሳስላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጦርነት ጊዜ ሰራዊቱ ሲጮኹ የሚያገሣ አንበሳ ይመስላሉ››

የአንበሳ ደቦል

ወጣትነት የብርታት መገለጫ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብርቱ አንበሳ››

ያደነቱንም ይዘው ይጮኻሉ

ጠላት የይሁዳን ሕዝብ መግደሉን አንበሳ ደካማውን እንስሳ ከመግደሉ ጋር ኢሳይያስ ያመሳስላል፡፡ ይህም ማለት 1) አንበሶች ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት ከፍ ያለ ጩኸት አያሰሙም፡፡ ወይም 2) ጸሐፊው በሁለት ቃላት የተጠቀመው አንድ ትርጒም ስላለው ነገር ለመናገር ነው፡፡

ንጥቂያ

አራዊት አድነው የሚዙት እንስሳ

የሚያስጥልም የለም

‹‹ማንም ሊያድናቸው አይችልም››

ያገሣሉ… እንደ ባሕር ሞገድ

እነዚህ ቃሎች ቁጥር 29 ላይ፣ ‹‹ይጮኻሉ›› በሚል የተተረጐሙት ናቸው፡፡ የባሕር ሞገድን ወይም ከባድ ዝናብን ወይም ሌላ አስፈሪ ተፈጥሮአዊ ድምፅን የሚመለክት ቃል በቋንቋህ ካለ ተጠቀምበት፡፡

ብርሃን እንኳ በደመናዎች ይጨልማል

እዚህ ላይ፣ ጨለማ መከራና ጥፋትን ይወክላል፡፡ ምሳሌያዊ ቋንቋውን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጨለማው ደመና የፀሐይ ብርሃንን ፈጽሞ ይጋርዳል››