am_tn/isa/05/27.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ይሁዳን ስለሚያጠቃው ሰራዊት መናገሩን ቀጥሏል፡፡ አሁን እንኳ እንደ መጣ አድርጐ ይናገራል፡፡ (ኢሳይያስ 5፥26 ይመ.)

ደካማ፣ ስንኩል፣ የሚያንቀላፉ፣ የሚተኛ

እነዚህ አራት ቃሎች በሥራ ከመድከም እስከ መራመድ አለመቻል፣ ንቁ ለመሆን ካለመቻል እስከ ሙሉ በሙሉ ንቁ አለ መሆን እያደጉ ይሄዳሉ፤ ስለዚህ ትርጒሙ ውስጥ አራቱም መኖር አለባቸው፡፡

ቀበቶአቸውንም አይፈቱም

በቀላሉ ተነሥተው መዋጋት እንዲያስችላቸው ወታደሮች ሁሌም ትጥቃቸው እንደ ተጠበቀ ነው፡፡

የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም

‹‹የጫማቸው ክር››

የፈረሶቻቸው ሸኾና እንደ ባልጩት ናቸው

‹‹ሸኾናቸው እንደ ጠንካራ ድንጋይ ነው›› ኢሳይያስ የፈረሶችን እግር ጠንካራ ክፍል ከተነካ የእሳት ብልጭታ ከሚወጣው ከጠንካራው ድንጋይ ከባልጩት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህም ማለት 1) ኢሳይያስ ሸኾናቸውን ከባልጩት ጋር ያመሳሰለው በሚሮጡበት ጊዜ የሚወጣውን ብልጭታ አስፈሪነት ለማሳየት ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም 2) ኢሳይያስን ሸኾናቸውን ከባልጩት ጋር ያመሳሰለው ፈረሶቹ ጌቶቻቸው የሚፈልጉትን ሁሉ ለማድረግ እንዲያስችላቸው ሸኾናቸው ምን ያህል ጠንካራ እንደ ሆነ ለማሳየት ሊሆን ይችላል፡፡

የሠረገሎቻቸው መንኩራኩሮች እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው

በመንገዳቸው የሚገኙትን ሁሉ እንደሚያጠፉ ለማሳየት ኢሳይያስ የሠረገሎቹን መንኮራኩር ከዐውሎ ነፋስ ጋር አመሳስሎታል፡፡

የሠረገሎች መንኮራኩሮች

ከእነዚህ መንኮራኩሮች ጋር የተያያዙ ስለታም ነገሮች አሉ፤ በአጠገቡ የሚያልፈውን ነገር ደቅቁታል፡፡