am_tn/isa/05/24.md

1.0 KiB

የእሳት ልሳኖች

‹‹የእሳት ነበልባል›› ወይም፣ ‹‹ነበልባል››

የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፣ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ

የእነዚህ ሐረጐች ትርጒም በመሠረቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢሳይያስ 5፥18-23 ላይ የተጠቀሱትን ሰዎች እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚያቃጥል››

ገለባ

እህል ከታጨደ በኃላ እርሻው ላይ የሚቀር ደረቅ የተክሎች አካል፡፡

ሥራቸው ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይሆናል

እነዚህ ሰዎች እንደ ሞቱ ተክሎች እንደ ሆነ ኢሳይያስ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሥሩ እንደበሰበሰ ተክል ይሞታሉ፤ ደርቆ በነፋስ እንደሚወሰድ አበባ ይበንናሉ››