am_tn/isa/05/13.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ቁጥሮች ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ያመለክታሉ፡፡

ሕዝቤ በምርኮ ተወስደዋል

በትንቢት ወደ ፊት የሚፈጸሙ ነገሮች ብዙውን ጊዜ አሁንእንደ ተፈጸሙ ተደርጐ ይነገራል፡፡ ይህ አጽንዖት የሚሰጠው ትንቢቱ በእርግጥ የሚፈጸም መሆኑን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከሌላ አገር የመጣ ጠላት ሕዝቤ እስራኤልን በባርነት ይወስዳል››

ዕውቀት በማጣት

ያላወቁት ምን እንደ ነበር ይበልጥ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌን ወይም ሕጉን አላወቁም››

ሲኦል ሆዷን አሰፋች፤ አፏንም ያለ ልክ ከፈተች

ይህ ሐረግ የሚናገረው በመቃብር ወይም ሌሎች እንስሳትን በሚበላ አውሬ ስለ ተመሰለው ስለ ሲኦል ነው፡፡ በጣም ብዙ ሰዎች እንደሚሞቱ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሞት ብዙ ሰዎችን ለመብላት እንደ ተራበ አውሬ አፉን በሰፊው ከፍቷል››

መኳንንቱ፣ ሕዝቡ፣ መሪዎቻቸውና ረብሸኞቻቸውና ጨፋሪዎቻቸው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ

ነቢዩ አሁን የተፈጸመ ይመሳል ስለ የወደ ፊቱ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብዙ የእስራኤል ሰዎች፣ ታላላቅና ታናናሾቻቸው፣ መሪዎቻቸውና ጭፈራን የሚወዱ ወደ ሲኦል ይወርዳሉ››