am_tn/isa/05/11.md

1.7 KiB

ማልደው ለሚነሡ… ሌሊቱን ለሚያነጉ

ይህ የሚያመለክተው አልኮል ከመጠጣት ውጪ ቀኑን ሙሉ ምንም ስለማይሠሩ ሰዎች ነው፡፡

እስኪያነጻቸው ወይን በመጠጣት

ጠጪዎቹን የሚያሰክር ወይን ጠጅ የሚያቃጥል ወይም የሚያነድ እሳት እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በወይን ጠጅ እስኪሰክሩ ድረስ››

በገና፣ መሰንቆ፣ ከበሮ፣ ዋሽንትና ወይን ጠጅ

እነዚህ የሙዚቃ መሣሪያዎችና ወይን ጠጅ ሰዎቹ በፈንጠዝያ ጊዜያቸውን እንደሚያሳልፉ ያመለክታሉ፡፡

ከበሮ

በእጅ የሚመታ፣ እንደ ታንቡር የሚመታ ራስ ያለው የሙዚቃ መሣሪያ፡፡ ምናልባትም ተጫዋቹ ሲንጣቸው ድምፅ የሚሰጡ የብረት ቁርጥራጮች ዙሪያውን ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ከበሮው ተጫዋቹ በአንድ እጁ ይዞ እስኪንጠው ድረስ በጣም ትንሽ ሊሆን ይችላል፡፡

አልሰጡም

አጥብቀው አላሰቡም

የእጆቹን ሥራ

‹‹ሥራ›› የሚለውን፣ ‹‹ያደረገውን›› ወይም፣ ‹‹የፈጠረውን›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ያደረገውን›› ወይም፣ ‹‹እርሱ የፈጠረውን››

የእጆቹን ሥራ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጆች›› አንዳች ነገር ያደረገ ሰውን ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ያደረገውን››