am_tn/isa/05/01.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ስለ ገበሬውና ስለ ወይን እርሻው ምሳሌ ይናገራል፡፡ ገበሬው ያህዌን፣ የወይን እርሻው ደቡባዊውን የእስራኤል መንግሥት የይሁዳን ሕዝብ ይወክላል፡፡

ወዳጄ

‹‹በጣም የምወደው››

በለመለመ ኮረብታ

‹‹መልካም ፍሬ በሚገኝበት ኮረብታ ላይ››

መሬቱን ቈፈረ

‹‹አፈሩን አዘጋጀ›› ይህ ለተክል ምቹ ለማድረግ መሬቱን በመቆፈሪያ መቆፈርን ያመለክታል፡፡

በመካከሉ ማማ ሠራ

‹‹ላዩ ላይ ሆኖ ለመጠበቅ በመካከሉ ረጅም ግንብ ሠራ›› የወይን እርሻውን ለመጠበቅ አንድ ሰው ማማው ጫፍ ላይ ሆኖ ሰዎች ወይም እንስሳት ወደዚያ እንዳይገቡ ይከላከላል፡፡ ይህን ዐረፍተ ነገር የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡

የወይን መጭመቂያ ጉድጓድም አበጀ

‹‹ወይኑን ለመጭመቅ ጉድጓድ ቆፈረ›› የወይን መጭመቂያ ሰዎች ወይን ፍሬውን እየረገጡ ጭማቂውን የሚያወጡበት መሬት ላይ ባለ ትልቅ ድንጋይ የተሠራ ነገር ነው፡፡

ኮምጣጣ ፍሬ

‹‹የማይጠቅም ፍሬ›› ወይም፣ ‹‹የማይጣፍጥ ፍሬ››