am_tn/isa/04/03.md

2.6 KiB

በጽዮን የቀሩት፤ በኢየሩሳሌም የተረፉት

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች አንድ ትርጒም ነው ያላቸው፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹የተረፉት›› ሲል ግለ ሰብን ሳይሆን በኢየሩሳሌም በሕይወት ያሉትን ሁሉ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኢየሩሳሌም የሚቀር ሁሉ››

ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ ቅዱሳን በማለት ይጠራቸዋል›› ወይም፣ ‹‹የጌታ ይሆናሉ››

በኢየሩሳሌም በሕይወት ከተመዘገቡት ሁሉ

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስሙ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መዝገብ ያለ ሰው ሁሉ››

ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ሲያጥብ

ይህ አባባል ኀጢአት እንደሚታጠብ እድፍ እንደ ሆነ ይናገራል፤ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ እድፍ እንደሚያጠራ፣ የጽዮንን ሴቶች ኀጢአት ካጠበ በኃላ››

የጽዮን ሴቶች

ይህ ማለት፣ 1) የኢየሩሳሌም ሴቶች፤ ወይም 2) የኢየሩሳሌም ሕዝብ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

ኢየሩሳሌምን ከተነከረችበት ደም ያነጻታል

‹‹የተነከረችበት ደም›› የሚያመለክተው ግፍንና ግድያን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ንጹሐንን የሚጐዱ የኢየሩሳሌምን ሰዎች ያስወግዳል››

በፍርድና መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ

እግዚአብሔር የኢየሩሳሌምን ኀጢአት የሚያስወግደው በዚህ መንገድ ነው፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹መንፈስ›› የፍርድና የማቃጠልን እንቅስቃሴ የሚወክል ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፍርድና በእሳት ነበልባል››

የፍርድ መንፈስ

ይህም ማለት 1) ያህዌ ሕዝቡን ይቀጣል፤ ወይም 2) ያህዌ ሕዝቡን በደለኛ ያደርጋል ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

በሚያቃጥል መንፈስ

ይህም ማለት 1) አንዳች ርኩስ ነገርን እንደሚስወግድ ያህዌ ኀጢአተኞችን ከጽዮን ያስወግዳል ማለት ሊሆን ይችላል፤ ወይም 2) ‹‹የሚያቃጥል እሳት›› የኀጢአተኞችን ሁሉ መደምሰስ ሊያመለክት ይችላል፡፡