am_tn/isa/03/24.md

1.8 KiB

ሻሽ

ሰዎች ወገባቸው ወይም ደረታቸው ላይ የሚለብሱት ልብስ፡፡ ኢሳይያስ 3፥20 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

ገመድ

ይህ የሚያመለክተው እነርሱን ሲይዟቸው ጠላቶቻቸው የይሁዳን ሰዎች የሚያስሩበትን ገመድ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ የኢየሩሳሌም ሴቶች በገመድ የሚታሰር ተራ ልብስ እንጂ፣ ሌላ ምንም የሚለብሱት እንደማይኖራቸው የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡

አምሮ በተሠራ ጠጉር ፈንታ ቡሀነት

‹‹ያመረ ጠጉር ቢኖራቸውም መላጣ ይሆናሉ››

ወንዶቻችሁ በሰይፍ፣ ይወድቃሉ ተዋጊዎቻችሁም በጦርነት ይወድቃሉ

መውደቅ መገደልን፣ ሰይፍ ጦርነትን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወንዶቻችሁ በጦርነት ይገደላሉ፤ ተዋጊዎቻችሁ በውጊያ ይገደላሉ›› ወይም፣ ‹‹ጠላቶች ወታደሮቻችሁን በጦርነት ይገድሏቸዋል››

የኢየሩሳሌም ደጆች ያዝናሉ ያለቅሳሉ

እዚህ ላይ የከተማው ደጆች ከተማው ደጃፍ ላይ አደባባይ የሚቀመጡ ሰዎችን ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የኢየሩሳሌም ሰዎች ከተማው በሮች ላይ ተቀምጠው ያዝናሉ ያለቅሳሉ››

ብቻዋን ትሆናለች መሬት ላይ ትቀመጣለች

ኢሳይያስ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ከጠላቶቿ የሚያድናት ሰው እንደሌላትና ወዳጆቿ ሁሉ ስለ ተውአት መሬት ላይ ተቀምጣ እንደምታለቅስ ሴት መሆናቸውን ይናገራል፡፡