am_tn/isa/03/18.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ክፍል ያህዌ በእንዴት ያለ ሁኔታ የኢየሩሳሌምን ሴቶች እንደሚቀጣ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ጌታ ይነጥቃቸዋል

ጌታ ሌሎች እንዲያደርጉ የሚያነሣሣው እርሱ የሚያደርገው እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ ሌሎች እንዲነጥቋቸው ያደርጋል››

የእግር ዐልቦ

ከእግር ከፍ ብሎ ቁርጭምጭሚታቸው ላይ ሴቶች የሚያደርጉት ጌጥ፡፡

የራስ መሸፈኛ

ሴቶች ራሳቸውና ጠጉራቸው ላይ የሚያደርጉት ጌጥ

የጨረቃ ቅርጽ ያለው የዐንገት ጌጥ

ሰዎችን ከክፉ ነገር ያድናል ብሎ በማሰብ ዐንገት ላይ የሚጠለቅ ባለ ጨረቃ ቅርጽ ጌጥ

የጆሮ ጉትቻ

ጆሮ ላይ የሚንጠለጠል ጌጥ

የእጅ አንባር

ሴቶች እጆቻቸው ላይ የሚያደርጉት ጌጥ

የፊት መሸፈኛ

የሴት ልጅን ፊትና ራስ የሚሸፍን በጣም ስስ ልብስ

የራስ መሸፈኛ

ሴቶች ራሳቸው ወይም ጠጉራቸው ላይ የሚያስሩት ረጅም ስስ ጨርቅ

ዐልቦ

ይህ ሴቶች ቁርጭምጭሚታቸው ላይ የሚያደርጉት ጌጥ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ደስ የሚል ድምፅ እንዲኖረው ሰንሰለት ይንጠለጠልበታል፡፡

ሻሽ

ሰዎች ወገባቸው ላይ የሚያደርጉት ጨርቅ

የሽቶ ብልቃጥ

መልካም ሽታ እንዲኖራቸው ሴቶች የሚቀቡት፣ በሰንሰለት ወይም በክር አንገታቸው ላይ የሚያንጠለጥሉት ብልቃጥ ወይም መያዣ

አሽንክታቡን

መልካም ዕድል እንዲያመጣ በማመን ሰዎች የሚያንጠለጥሉት ጌጥ