am_tn/isa/03/10.md

3.0 KiB

ጻድቃን መልካም ነገር እንደሚያገኙ ንገራቸው

‹‹ተገቢ የሆነውን ለሚያደርጉ እኔ መልካም ነገር እንደማደርግላቸው ንገራቸው››

ጻድቃን ሰዎች

ይህ በአጠቃላይ ጻድቃን ሰዎችን ይመለከታል፤ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጻድቃን የሆኑ ሰዎች››

የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና

ሥራ ሰዎች የሚበሉት ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ፍሬ የመልካም ሥራ ሽልማትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የመልካም ሥራቸውን ሽልማት ይቀበላሉና›› ወይም፣ ‹‹ስላደረጉት መልካም ሥራ ሽልማት ይቀበላሉ››

የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና

የዕብራይስጡ ምንባብ እዚህ ላይ በብዙ ቁጥር በሚያመለክት ተውላጠ ስም ይናገራል፤ ይሁን እንጂ ማንኛውንም ጻድቅ ሰው ይመለከታል፡፡ ተርጓሚዎች በነጠላ ቁጥር መተርጐም ይችላሉ፡- ‹‹የሥራውን ፍሬ ይበላል››

የእጁን ያገኛል

እዚህ ላይ ‹‹እጅ›› ሰው የሚያደርገውን ሥራ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክፉ ሰው ሌሎች ላይ እንደሚያደርገው ይደረግበታል፡፡››

ሕዝቤ… ሕዝቤ

ይህም ማለት 1) ኢሳይያስ እየተናገረ ነው፤ ‹‹የእኔ›› የሚለው የሚያመለክተው ኢሳይያስን ነው፤ ወይም 2) ያህዌ እየተናገረ ነው፤ ‹‹የእኔ›› የሚለው የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡

ልጆች ጨቋኞቻቸው ናቸው

ይህም ማለት 1) ‹‹ወጣቶች መሪዎቻቸው ሆኑ፤ እነርሱም ሕዝቡን ይጨቁናሉ›› ወይም 2) ‹‹መሪዎቻቸው እንደ ልጆች ያልበሰሉ ናቸው፡፡ ሕዝቡንም ይጨቁናሉ››

ሴቶችም ይገዟቸዋል

ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ሴቶች ሕዝቡን ይገዛሉ›› ወይም 2) ‹‹መሪዎቻቸው እንደ ሴቶች ደካሞች ናቸው››

መሪዎችህ አሳስተውሃል፤ ከመንገድም መልሰውሃል

በጥንታዊው መካከለኛው ምሥራቅ የሕዝብ መሪዎች እረኞች እንደ ሆኑ መናገር የተለመደ ነበር፡፡ እረኞች በጐቹን ለመመገብ በመልካም መንገድ ወደ ደህና ቦታ እንደሚመሩ፤ መሪዎችም ሕዝቡን እውነቱን ማስተማርና መልካም እንዲያደርጉ ማስተማር ይኖባቸዋል፡፡ የይሁዳ መሪዎች ይህን እያደረጉ አልነበረም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መሪዎችህ ከመልካም መንገድ የሚመልሱህ መጥፎ እረኞች ናቸው፤ ወዴት መሄድ እንዳለብህም አላሳዩህም››