am_tn/isa/03/08.md

1.7 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ነቢዩ በዚህ ሁኔታ ላይ ሐሳብ መስጠት ቀጥሏል፡፡

ኢየሩሳሌም ተሰናከለች፤ ይሁዳም ወደቀች

ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ተሰናክሎ መውደቅ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የክብሩ ዐይን

‹‹ዐይን›› ክቡር የሆነውን ራሱ እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክቡር የሆነው እርሱ›› ወይም፣ ‹‹ክቡር የሆነው ያህዌ››

የፊታቸው ገጽታ ይመሰክርባቸዋል

ሰዎች ፊት ላይ የሚታየው እብሪት፣ የሰዎቹን ኩራት እንደሚመሰክርባቸው ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ፊታቸው ላይ የሚታየው እብሪት ያህዌን እንደሚቃወሙ ያሳያል››

ኀጢአታቸውን እንደ ሰዶም በይፋ ይናገራሉ፤ አይደብቁትምም

በኀጢአታቸው ስለሚኩራሩ እዚህ ላይ የይሁዳ ሰዎች እንደ ሰዶም ሰዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ሰዶም ሰዎች ሰው ሁሉ እንዲያውቅላቸው ስለ ኀጢአታቸው ያወራሉ››

ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ

አሁንም ቢሆን ጥፋት እየመጣ ነው፤ ሕዝቡ ግን እንዲመጣ ጥፋት የሚያደርገውን ሁሉ አድርገው ጨርሰዋል፡፡ የጥፋቱ መምጣት ምክንያት ራሱ ጥፋቱ እንደ ሆነ እዚህ ላይ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጥፋት እንዲመጣ ምክንያት የሆነውን ሁሉ አድርገው ጨርሰዋል››