am_tn/isa/03/06.md

976 B

ይህን ፍርስራሽ በእጅህ አድርግ

‹‹እጅ›› ሥልጣንን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚህ ፍርስራሽ ላይ ኀላፊ ሁን›› ወይም፣ ‹‹በዚህ ፍርስራሽ ላይ ግዛ››

ይህን ፍርስራሽ

ይህ ማለት የሚከተሉትን ማለት ሊሆን ይችላል፤ 1) ብዙዎቹ የኢየሩሳሌም ሕንፃዎች ፈራርሰው ነበር፡፡ ወይም 2) የኢየሩሳሌም ሰዎች ሀብት ወይም መሪ አልነበራቸውም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሁን የፈረሰው ይህ ከተማ››

ፈዋሽ አልሆንም

የሰዎችን ችግር መፍታት እነርሱን መፈወስ እንደ ሆነ ተነግሮአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፍጹም፤ እኔ ይህን ችግር መፍታት አልችልም›› ወይም፣ ‹‹የለም፤ እኔ ልረዳችሁ አልችልም››