am_tn/isa/03/01.md

2.0 KiB
Raw Permalink Blame History

እነሆ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እነሆ›› ለሚከተለው አጽንዖት ይሰጣል፡፡ ‹‹ተመልከቱ›› ወይም፣ ‹‹በእርግጥ›› ተብሎ ሊተረጐምም ይችላል፡፡

ድጋፍና ርዳታ

ሁለቱም የሚያመለክቱት ሰዎች የሚደገፉበትን ምርኩዝ ነው፡፡ እዚህ ላይ የሚያመለክተው በሕይወት ለመኖር ሰዎች በጣም የሚፈልጉትን ነገር እህልና ውሃን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ድጋፍ የሚሆናችሁን ነገር ሁሉ›› ወይም፣ ‹‹የምትተማመኑበትን ነገር ሁሉ››

ጀግናው… ብልኁልና አስማተኛውን

ይህ አንዳንድ ሰዎች የሚደገፉባቸው ነገሮች ዝርዝር ነው፡፡ ስለ የትኛውም ዐይነት ግለሰብ እንደ ተነገረ ስለሚያመለክቱ UDB ላይ እንዳለው በብዙ ቁጥር መተርጐም አለበት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተዋጊ ሰዎች… ብልኅ አስማተኞች››

ጥንቆላ የሚለማመድ

ይህ የእንስሳትን አካል ክፍሎች ወይም ቅጠሎችን የመሳሰሉ ነገሮች በማየት የወደ ፊቱን መናገር እችላለሁ የሚል ሰው ነው፡፡ ኢሳይያስ 2፥6 ላይ ያለውን ተመሳሳይ ቃል እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

የአምሳ አለቃው

ይህ የሚከተለውን ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ 1) ‹‹አምሳ›› የሚለው ቃል ሰውየው የሚመራቸውን ሰዎች ቁጥር ያመለክት ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ የ50 ወታደሮች አለቃ›› ወይም 2) ‹‹አምሳ›› ተብሎ የተተረጐመው ቃል የአነስተኛ ወታደራዊ ምድብ ስም እንጂ፣ ትክክለኛ ቁጥርን አይወክልም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአነስተኛ ወታደራዊ ምድብ ኀላፊ››

አምሳ

50