am_tn/isa/02/14.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡ በሰራዊት ጌታ በያህዌ ቀን የሚሆነውን በተመለከተ ገለጻውን ቀጥሏል፡፡

በ… ላይ

2፥14-16 እግዚአብሔር የሚያጠፋቸውን ነገሮች ይዘረዝራል፡፡ ይህም የሚከተሉትን ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ 1) እግዚአብሔር የሚያዋርዳቸውን ክፉ ሰዎች ያመለክታል፡፡ ወይም 2) እግዚአብሔር ዝርዝሩ ውስጥ የተጠቀሱ ነገሮች ሁሉ ያጠፋል፡፡

ተራሮች… ኮረብቶች

እነዚህ ቃሎች ትዕቢተኛ እስራኤላውያንን ያመለክታሉ፡፡ ኢሳይያስ 2፥2 ላይም ይገኛሉ፡፡

ከፍ ያለው ሁሉ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም ከፍ ያለው››

ረጅሙ ግንብ… የተመሸገው ቅጥር

ይህ የሚያመለክተው ራሳቸውን ከጠላቶቻቸው ለመከላከል ሰዎች ከተሞቻቸው ዙሪያ የሚሠሩዋቸውን ግንቦች ነው፡፡ የእስራኤላውያን ትዕቢትና ያህዌን አታስፈልገንም ማለታቸው ለኀጢአታቸው ያህዌ የሚያመጣባቸውን ቅጣት ሁሉ መቋቋም እንደሚችሉ የማሰባቸው ምሳሌ ነው፡፡

የተመሸገው ቅጥር

‹‹ምንም የማያፈርሰው ወይም የማይሻገረው››

የተርሴስ መርኮቦች… ያማሩ ጀልባዎች

እነዚህ የሚያመለክቱት ሰዎች በባሕር ላይ ርቀው በመሄድ የተለያዩ ነገሮችን ወደ ከተሞቻቸው ለማምጣት የሚጠቀሙባቸውን መጓጓዣዎች ነው፡፡

የተርሴስ መርከቦች

‹‹ወደ ተርሴስ የሚሄዱባቸው መርከቦች››