am_tn/isa/02/12.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

ረጅምና ከፍ ከፍ ያሉትን

‹‹ከፍ ያለ ሰው›› ትዕቢተኛና ከሌሎች የበለጠ እንደ ሆነ የሚያስብ ሰው ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ትዕቢተኛና ራሱን ከሌሎች በላይ ከፍ የሚያደርግ ሰው›› ወይም፣ ‹‹ትዕቢተኛና ከሌሎች የበለጠ እንደ ሆነ የሚያስብ ሰው››

ትዕቢተኛና እብሪተኛ

እብሪተኛ የሆነ ሰው ከሌሎች የበለጠ መሆኑን ይናገራል፡፡ እነዚህ ሁለት ሐረጐች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፤ በአንድነት የቀረቡት ያህዌ እንደሚቀጣቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

ይዋረዳል

‹‹ማንኛውም ትዕቢተኛ ይዋረዳል›› ይህን በተሻለ ሁኔታ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ያዋርደዋል››

የሊባኖስ ዝግባዎች ሁሉ… የባሳንን የወርካ ዛፍ ሁሉ

‹‹የሰራዊት ጌታ የያህዌ ቀን›› በዝግባዎችና በወርካዎች ላይ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የሚከተሉትን ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ 1) እነዚህ ዛፎች ያህዌ የሚፈርድባቸው ትዕቢተኞች ምሳሌ ናቸው፡፡ ወይም 2) እግዚአብሔር እነዚህ ግዙፍ ዛፎችን ያጠፋል፡፡