am_tn/isa/02/09.md

3.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

2፥9 ላይ ኢሳይያስ ለያህዌ መናገሩን ያበቃል፡፡ 2፥10-11 ላይ ኢሳይያስ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡ ሁለቱንም ጊዜ የሚናገረው በቅኔ መልክ ነው፡፡

ሰዎች ዝቅ ብለዋል፤ ግለ ሰቦችም ወድቀዋል

እዚህ ላይ ሰዎች ወደ መሬት ዝቅ ማለታቸው የሚያመለክተው የታመኑበት ሁሉ ከንቱ መሆኑንና ራሳቸውንም ለመርዳት ምንም ማድረግ አለመቻላቸውን በመረዳታቸው በጣም መዋረዳቸውን ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር ሰዎችን ያዋርዳል፤ የታመኑበት ሁሉ ከንቱ መሆኑንም ይረዳሉ››

ሕዝቡ

ከእንስሳት የተለዩ ሰብዓዊ ፍጡራን

ግለ ሰቦች

‹‹እያንዳንዱ ሰው››

ከእንግዲህ አታንሣቸው

‹‹አታንሣቸው›› የሚለው ያህዌ ሕዝቡን ይቅር የማለቱ ምሳሌ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይቅር አትበላቸው››

ወደ ዐለቶች ሂድ

ይህ የሚከተሉትን ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ 1) ሰዎች ኮረብቶች ላይ ወዳሉ ዐለቶች መሄድ አለባቸው ወይም 2) መደበቅ የሚችሉበት ብዙ ዐለቶች ያሉበት ቦታ፡፡

በመሬት ውስጥ ተሸሸግ

ይህ የሚከተሉትን ማለት ሊሆን ይችላል፤ 1) መሬት ውስጥ ባሉ ጉድጓዶች መደበቅ ወይም 2) መሬት ውስጥ በቆፈሩት ጉድጓድ፡፡

ከያህዌ አስፈሪነት

እዚህ ላይ ‹‹አስፈሪ›› የሚለውን፣ ‹‹አስደንጋጭ›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከአስደንጋጭ የያህዌ ፊት ለመሸሽ›› ወይም፣ ‹‹በጣም ከምትፈሩት ከያህዌ››

የግርማው ክብር

‹‹እንደ ንጉሥ እርሱ ያለው ውበትና ኀይል›› ወይም፣ ‹‹ንጉሣዊ ክብሩ›› ኢሳይያስ 2፥10 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

የዕብሪተኛ ዐይን ይሰበራል

‹‹ያህዌ የሰዎችን እብሪት ያዋርዳል›› ‹‹የሰዎች እብሪት ዐይን›› ከሰዎች ሁሉ በላይ ሆኖ መታየት ከእነርሱ የተሻለ እንደሆነ ማሰብ ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ከያህዌ የተሻሉ እንደሆኑ በማሰብ ሰዎች ሁሉ በደል ፈጽመዋል፤ ያህዌን የሚያመልኩትን የሚያዩበት ሁኔታ የትዕቢታቸው መገለጫ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእርሱ የተሻሉ እንዲሆኑ በማሰባቸው ያህዌ ሰዎችን ሁሉ ያሳፍራል››

የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል

‹‹የሰዎች ትዕቢት›› ትዕቢተኞችን ይወክላል፤ ‹‹ይሰበራል›› ዝቅ ይላል ወይም ያፍራል ማለት ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ትዕቢተኞችን ያዋርዳል›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ትዕቢተኞች በራሳቸው እንዲያፍሩ ያደርጋል››

ያህዌ ብቻውን ከፍ ይላል

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ያህዌን ብቻ ያመሰግናሉ››

በዚያን ቀን

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚያ ቀን ያህዌ በሁሉም ላይ ይፈርዳል››