am_tn/isa/02/03.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

እንዲያስተምረን ያዕቆብ… እንሄዳለን

ሌላው ትርጒም፣ ‹‹ያዕቆብ ያስተምረናል… እኛም እንሄዳለን››

እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጐዳናውም እንሄዳለን

‹‹መንገድ›› እና፣ ‹‹ጐዳና›› የሰውን አኗኗር የሚያመለክቱ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በቋንቋህ ሰዎች ስለሚሄዱበት መንገድ ያላችሁ ቃል አንድ ብቻ ከሆነ ሁለቱን እንደ አንድ ቃል ልትጠቀምባቸው ትችላለህ፡፡

ሕግ ከጽዮን፣ የያህዌም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣል

ሁለቱም ሐረጐች የሚያመለክቱት ተመሳሳይ ነገርን ነው፡፡ እውነት በኢየሩሳሌም መገኘቱን ሰዎች ሁሉ እንደሚረዱ ኢሳይያስ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጽዮን ያሉ የእግዚአብሔርን ሕግ፣ በኢየሩሳሌም የሚኖሩም የያህዌን ቃል ያስተምራሉ››

ከጽዮን ሕግ ይወጣልና

‹‹ሕግ ከጽዮን ይወጣልና›› ሕጉ ሰዎች ምንም ሳያደርጉ እንደ ወንዝ የሚወጣ ነገር መሆኑን ኢሳይያስ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለሚያስተምሯቸው ሰዎች ሕጉ ከጽዮን ይወጣላቸዋል›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ከጽዮን ሕጉን ይናገራል››

የያህዌ ቃል ከኢየሩሳሌም

‹‹የያህዌ ቃል ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ይሄዳል›› የያህዌ ቃል ሰዎች ምንም ሳያደርጉ እንደ ወንዝ የሚሄድ ነገር እንደ ሆነ ኢሳይያስ ይናገራል፡፡ በውስጠ ታዋቂነት ያለውን መረጃ የበለጠ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለሚያስተምሯቸው ሰዎች ከኢየሩሳሌም የያህዌ ቃል ይወጣላቸዋል›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ቃሉን ከኢየሩሳሌም ይናገራል››