am_tn/isa/02/01.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ የያህዌ ቃል ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

ይሁዳና ኢየሩሳሌም

‹‹ይሁዳ›› እና፣ ‹‹ኢየሩሳሌም›› እዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ››

በመጨረሻዎቹ ቀኖች

‹‹ወደ ፊት››

የያህዌ ቤት ተራራ ይመሠረታል

ይህም ማለት 1) ገለጻ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የያህዌ ቤት ተራራ ጸንቶ ይቆማል›› ወይም 2) በሌላ መልኩ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቤተ መቅደሱ የሚሠራበትን ተራራ ያህዌ ይመሠርታል››

በተራሮችም ከፍታ ላይ

ያህዌ ግዙፍ ከፍታን በመሰለ ሁኔታ ስለ አስፈላጊነቱ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም አስፈላጊ የሆኑ ተራሮች›› ወይም፣ ‹‹በዓለም ላይ በጣም አስፈላጊ የሆነ ቦታ››

ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ይላል

ኢሳይያስ ከፍታን በመጠቀም በምሳሌያዊ መንገድ ስለ ክብር ይናገራል፡፡ ይህንን በሚከተለው ሁኔታ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ 1) አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ከሌላው ኮረብታ የበለጠ ያከብረዋል›› ወይም፣ እዚያ የሚያመልኩ ሰዎችን ለማመልከት፣ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሌሎች ሰዎችን ካከበረው የበለጠ ያህዌ እዚያ የሚያመልኩትን ሰዎች ያከብራል››

ሕዝቦች ሁሉ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ሕዝቦች›› በእነዚህ አገሮች የሚኖሩ ሰዎች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከአገሮች ሁሉ የመጡ ሕዝቦች››

ይጐርፋሉ

ወደ ያህዌ ተራራ የሚሄዱ ሰዎች ከጐርፍ ጋር ተመሳስለዋል፡፡ ይህም ጥቂት ሳይሆኑ ብዙ ሰዎች እንደሚመጡ አጽንዖት ለመስጠት ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ወንዝ ወደ እርሱ ይጐርፋሉ›› ወይም፣ ‹‹ወደ እርሱ ይሄዳሉ››