am_tn/isa/01/29.md

886 B

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ የያህዌን ቃል ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

የተቀደሱ ወርካ ዛፎች… አትክልት ቦታዎች

እነዚህ ሐረጐች የይሁዳ ሕዝብ ጣዖት ያመለኩባቸውን ቦታዎች ያመለክታሉ፡፡

በ… ታፍራላችሁ

አንዳንድ ቅጂዎች፣ ‹‹ከዚህ የተነሣ ትደነግጣላችሁ›› ይላሉ፡፡ አንድ ሰው መጥፎ ነገር እንዳደረገ ሲሰማው ይደነግጣል ፊቱ ይቀላል፡፡

ቅጠሉ እንደ ጠወለገ ወርካ፣ ውሃም እንደሌለው የአትክልት ቦታ ትሆናላችሁ

ውሃ ለዛፎችና ለአትክልት ቦታዎች ሕይወት ይሰጣል፡፡ ሕዝቡ ሕይወት ከሚሰጣቸው ከያህዌ ራሳቸውን ለይተዋል፡፡