am_tn/isa/01/27.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ የያህዌን ቃል ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

ጽዮን በፍትሕ፣ በንስሐ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ የበለጠ ግልጽ ማድረግም ይቻላል፡፡ እንዲህ ማለት ሊሆን ይችላል፤ 1) ‹‹እዚያ ያሉ ሰዎች ትክክለኛ ነገር በማድረጋቸው ያህዌ ጽዮንን ይዋጃል፤ ያህዌ ትክክል የሚለውን በማድረጋቸው በንስሐ የሚመለሱትን ያህዌ ያድናል›› ወይም 2) ‹‹እርሱ ጻድቅ ስለሆነ ያህዌ ጽዮንን ይዋጃል፤ ጻድቅ ስለሆነም በንስሐ የሚመለሱትን ያድናል››

ጽዮን

ይህ በጽዮን ተራራ የሚኖሩ ሰዎች መጠሪያ ነው፡፡

ዐመፀኞችና ኀጢአተኞች በአንድነት ይደቅቃሉ

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእርሱ ላይ የሚያምፁትንና ኀጢአት የሚያደርጉትን ያህዌ ያጠፋቸዋል››

ያህዌንም የሚተዉ ይጠፋሉ

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእርሱ የሚመለሱትን ያህዌ ፈጽሞ ያጠፋቸዋል›› ወይም፣ ‹‹እርሱን ችላ የሚሉትን ያህዌ ይገድላቸዋል››