am_tn/isa/01/23.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ የያህዌን ቃል ለሕዝቡ እየተናገረ ነው፡፡

ገዢዎቻችሁ ዐመፀኞች ሆነዋል

‹‹መሪዎቻችሁ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀዋል፡፡››

የሌቦች ግብረ አበር

‹‹ከሌሎች የሚሰርቁ ሰዎች ጓደኞች ሆነዋል››

ጉቦ… እጅ መንሻ

መሪዎቹ ፍርድ እንዲያጣምሙላቸው ሕዝቡ ለክፉ መሪዎች፣ ‹‹ጉቦ›› ይሰጣሉ፡፡ ሕጉን በመተላለፍ ጥቅም እንዲያገኙ መሪዎች፣ ‹‹እጅ መንሻ ይቀበላሉ፡፡››

እጅ መንሻን በብርቱ ይፈልጋሉ

ጉቦ እንዲሰጠው በብርቱ የሚፈልግ ሰው እጅ መንሻ ከእርሱ ከሚሸሽና ያንን ለመያዝ ከሚሮጥ ሰው ጋር ተመሳስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እውነተኛ ያልሆነ ፍርድ ለማድረግ ሰው ሁሉ አጥብቆ ገንዘብ እንዲከፈለው ይፈልጋል››

አባት ለሌላቸው አይቆሙም

‹‹አባት ለሌላቸው አይሟገቱም››

የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም

‹‹በሕግ ተላላፊዎች ላይ እንዲፈርዱላቸው መበለቶች ወደ እነርሱ ሲመጡ አይሰሟቸውም›› ወይም፣ ‹‹ከሕግ ተላላፊዎች እንዲያስጥሏቸው መበለቶች ወደ እነርሱ ሲመጡ አይረዷቸውም››