am_tn/isa/01/21.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት…

ይህ ቃለ አጋኖ የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በተመለከተ ኢሳይያስ ያደረበትን ቁጣና ሐዘን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእግዚአብሔር ታማኝ የነበሩት የኢየሩሳሌም ሕዝብ ላይ የሆነውን ተመልከቱ››

አመንዝራ ሆነች

ኢሳይያስ ሕዝቡን ለባልዋ ታማኝ ካልሆነች፣ ነገር ግን ገንዘብ ለማግኘት ከሌሎች ወንዶች ጋር ከምትተኛ ሴት ጋር ያመሳስላቸዋል፡፡ ሕዝቡ ሐሰተኛ አማልክት አመለኩ እንጂ፣ ለእግዚአብሔር ታማኝ አልሆኑም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ አመንዝራ ሆኑ››

ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት ከተማ

‹‹እርሷ›› የሚለው ኢየሩሳሌምና ሕዝቧን ያመለክታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከተሞችን ከሴቶች ጋር ያመሳስላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የኢየሩሳሌም ሕዝብ መልካም ነበሩ፤ መልካም ነገርንም ያደርጉ ነበር››

አሁን ግን ነፍሰ ገዳዮች የሞሉባት ሆነች

‹‹እርሷ›› የሚለው ኢየሩሳሌምንና ሕዝቧን ያመለክታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከተሞችን ከሴቶች ጋር ያመሳስላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሁን ግን የኢየሩሳሌም ሰዎች ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ››

ብርሽ ዝጐአል፤ የወይን ጠጅሽ ከውሃ ጋር ተቀላቀለ

እዚህ ላይ ኢሳይያስ ብርና ወይን ጠጅን - ከሚከተሉት ጋር ያመሳስላል 1) ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ጋር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ንጹሕ እንዳልሆነ ብር፣ ከውሃ ጋር እንደ ተቀላቀለ ወይን ጠጅ ሆናችኃል›› ወይም 2) ሕዝቡ ቀድሞ ያደረግ ከነበረው መልካም ነገር ጋር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቀድሞ መልካም ነገር ታደርጉ ነበር አሁን ግን መልካም ሥራችሁን ከንቱ የሚያደርግ ነገር እያደረጋችሁ ነው››

የዛገ… ብር

ብር በየጊዜው መንጻት አለበት፤ አለበለዚያ ደምቆ አይታይም፡፡

ወይን ጠጅ… ውሃ

ውሃ የበዛበት ወይን ጠጅ በጣም አይጣፍጥም፤ እንዲያውም ከውሃ አይሻልም፡፡