am_tn/isa/01/19.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር አሁንም ለይሁዳ ሕዝብ እየተናገረ ነው፡፡

እሺ ብትሉ ብትታዘዙም

‹‹እሺ›› ማለት እና፣ ‹‹መታዘዝ›› ጥቅም ላይ የዋሉት አንድን ሐሳብ ለመግለጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፈቃደኝነት ብትታዘዙ››

የምድርን በረከት ትበላላችሁ

‹‹ምድሪቱ የምትበሉት በረከት ትሰጣችኃላችሁ››

እንቢ ብላችሁ ብታምፁ ግን

‹‹አልሰማም ብላችሁ እኔ ላይ ብታምፁ››

ሰይፍ ይበላችኃል

‹‹ሰይፍ›› የሚያመለክተው የይሁዳን ጠላቶች ነው፡፡ ‹‹ይበላችኃል›› የሚለውም ቃል የይሁዳን ጠላቶች ሌላውን እንስሳ ከሚያጠቁና ከሚበሉ አራዊት ጋር ያመሳስላቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቻችሁ ይገድሏችኃል››

የያህዌ አፍ ይህን ተናግሮአል

‹‹አፍ›› የሚለው ቃል ያህዌ መናገሩንና የተናገረውም በእርግጥ የሚፈጸም መሆኑን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ተናግሮአል›› ወይም፣ ‹‹ይህ እንደሚፈጸም ያህዌ ተናግሮአል››