am_tn/isa/01/18.md

2.3 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ አሁንም ለይሁዳ ሕዝብ እየተናገረ ነው፡፡

ኑና…

ቃሉን እንዲሰሙ ያህዌ በቸርነትና በፍቅር ሰዎችን ይጣራል፡፡ ‹‹እኔን ስሙ፤ ኑና›› ወይም፣ ‹‹ልብ በሉ፤ ልረዳችሁ እፈልጋለሁ፤ ኑና››

ኑና እንዋቀስ

‹‹በአንድነት ስለዚህ ጉዳይ እናስብ›› ወይም፣ ‹‹እዚህ ላይ እንወያይ›› ወይም፣ ‹‹ታዲያ፣ ምን ማድረግ አለብን? ስለ ወደ ፊቱ እንዲወያዩ ያህዌ ሕዝቡ ይጠራል፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹እኛ›› የሚለው ያህዌንና የይሁዳን ሕዝብ ይወክላል፡፡

ኃጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል

ሕዝቡ እንደ ባዝቶ መንጻት የነበረበትን ልብስ እንደ ለበሱና ኀጢአታቸውም ልብስ ላይ እንዳረፈ ቀይ ጠብታ እንደ ሆነ ኢሳይያስ ይናገራል፡፡ ያህዌ ኀጢአታቸውን ይቅር ካለ ልብሳቸው እንደ ገና ይነጣል፡፡

እንደ ዐለላ

ዐለላ ደማቅ ቀይ ቀለም ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ደማቅ ቀይ››

እንደ በረዶ ይነጣል

ብዙውን ጊዜ ነጭ የቅድስናና የንጽሕና ምልክት ነው፡፡ ‹‹በረዶ›› ወደ ጠጣርነት የተለወጠ በጣም ነጭ ነገርን ያመለክታል፡፡ ይህ የሚያሳየው በጣም ነጭ የሆነ ነገርን በመሆኑ ነጭ በሆነ ሌላ ነገር መተካት ትችላላችሁ፤ ‹‹እንደ ኖራ ነጭ›› ወይም፣ ‹‹እንደ ርግብ ነጭ›› ይህም ማለት ኀጢአታቸው ይቅር ይባላል ማለት ነው፡፡

እንደ ዐለላ ቢቀላ

ዐለላ ደብዛዛ ቀይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ደብዛዛ ቀይ››

እንደ ባዘቶ

ባዘቶ የበግ ወይም የፍየል ጠጉር ነው፡፡ እንደ ባዝቶ መንጻትን በተመለከተ የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ባዘቶ ነጭ››