am_tn/isa/01/12.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ የያህዌን ቃል ይናገራል፡፡

ይህን ሁሉ እንድታመጡ፣ የመቅደሴን ደጅ እንድትረግጡ የጠየቃችሁ ማን ነው?

‹‹መርገጥ›› አንድ ነገር ላይ ቆሞ በእግሮች መጨፍለቅ ማለት ነው፡፡ በይሁዳ የሚኖሩ ሰዎችን ለመገሠጽ እግዚአብሔር በጥያቄ ይጠቀማል፡፡ ይህን ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የመቅደሴን ደጅ እንድትረግጡ የጠየቃችሁ የለም፡፡››

ከንቱ መባ አታምጡ

‹‹ከንቱ ስጦታዎቻችሁን አታምጡልኝ››

ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ

‹‹እጸየፋለሁ›› የሚለውን ቃል፣ ‹‹እጠላለሁ›› በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ካህናት የሚያጨሱትን ዕጣን እጠላለሁ››

እነዚህ ክፋት የሞላባቸው ጉባኤዎቻችሁን መታገሥ አልችልም

ይህም ማለት፤ 1) ‹‹ከምታደርጓቸው ክፉ ነገሮች የተነሣ እንድትሰበሰቡ አልፈቅድላችሁም›› ወይም 2) ‹‹ከምታደርጓቸው ክፉ ነገሮች የተነሣ ስብሰባችሁን ማየት አልፈልግም››