am_tn/isa/01/10.md

959 B

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

እናንተ የሰዶም ገዦች… እናንተ የገሞራ ሰዎች

ምን ያህል ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ ለማሳየት ኢሳይያስ የይሁዳን ሕዝብ ከሰዶምና ከገሞራ ሕዝብ ጋር ያነጻጽራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እናንተ እንደ ሰዶም ሕዝብ ኀጢአተኞች የሆናችሁ ገዦች… እናንተ በገሞራ እንደሚኖሩ ዐመፀኛ የሆናችሁ ሰዎች››

የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምኔ ነው?

የእስራኤልን ሕዝብ ለመገሠጽ እግዚአብሔር በጥያቄ ተጠቅሟል፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብዙ መሥዋዕት ማቅረባችሁ ለእኔ ምንም ማለት አይደለም››