am_tn/isa/01/09.md

862 B

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

ያህዌ… ኖሮ

ይህ የሚያመለክተው ባለፈው ጊዜ መሆን የነበረበትን፣ ግን ያልሆነ ነገርን ነው፡፡

ትንሽ ትሩፍ

‹‹የተረፉ ጥቂቶች››

የእኛ… እኛ

እነዚህ ቃሎች የሚያመለክቱት ኢሳይያስን ሲሆን፣ የይሁዳና የኢየሩሌምንም ሕዝብ ይጨምራል፡፡

እንደ ሰዶም በሆንን፣ ገሞራንም በመሰልን

ይሁዳ እንደ ሶዶምና እንደ ገሞራ ሊሆን ይችል የነበረበትን ምክንያት ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዶምና ገሞራን እንዳጠፋ እግዚአብሔር ያጠፋን ነበር››