am_tn/isa/01/07.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

አገራችሁ ጠፍቷል

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አገራችሁን አጥፍተዋል›› ወይም፣ ‹‹ጠላቶቻችሁ አገራችሁን አጥፍተዋል››

ከተሞቻችሁ ተቃጥለዋል

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከተሞቻችሁን አጥፍተዋል››

እርሻዎቻችሁን በፊታችሁ እንግዶች ያጠፏቸዋል፡፡

‹‹የአገራችሁ ያልሆኑ ሰዎች ዐይናችሁ እያየ እህላችሁን ከእርሻዎቻችሁ ይወስዳሉ››

ጠፍ ሆኖ ይቀራል

‹‹ባዶና የፈረሰ›› ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምድሩን አጥፍተዋል፤ ማንም አይኖርበትም››

በባዕድ ይነጠቃል

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ባዕዳን አገራችሁን ይነጥቃሉ›› ወይም፣ ‹‹የሌላ አገር ሰራዊት ጨርሶ ድል አድርጐታል››

የጽዮን ሴት ልጅ ተተወች

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጽዮንን ሴት ልጅ ትቻታለሁ››

የጽዮን ሴት ልጅ

የከተማ፣ ‹‹ልጅ›› የዚያ ከተማ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጽዮን ሕዝብ›› ወይም፣ በጽዮን የሚኖር ሕዝብ››

በወይን አትክልት ውስጥ እንዳለ ዳስ፣ በዱባ ተክል ውስጥ እንደሚገኝ ጐጆ ተተወች

ይህም ማለት 1) ‹‹የወይን ተክል ውስጥ እንዳለ ዳስ፣ የዱባ ተክል ውስጥ እንደሚገኝ ጐጆ አነሰች›› ወይም፣ 2) ‹‹ገበሬ ጉዳዩን ስጨርስ እንደሚተወው ወይን ተክል ውስጥ እንዳለ ዳስ የዱባ እርሻ ውስጥ እንዳለ ጐጆ ተተወች››

እንደ… ዱባ፤ እንደ ተከበበ ከተማ

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ‹‹እንደ… ዱባ እንደ ተከበበ ከተማ ሆነች››