am_tn/isa/01/04.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

ሕዝብ፣ ኀጢአተኛ

በሌላ መልኩ፣ 1) ኢሳይያስ ስለ እነርሱ ሁለት የተለያዩ ነገሮች እየተናገረ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ፣ እናንት ኀጢአተኞች›› ወይም፣ 2) ስለ እነርሱ አንድ ነገር ብቻ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀጢአተኛ ሕዝብ››

ርኩሰት የተጫነው ሕዝብ

ሰው የሚሸከመው ከባድ ሸክም፣ የብዙ ኀጢአታቸው ምሳሌ ሆኗል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀጢአታቸው ጀርባቸው ላይ እንደ ተሸከሙት ከባድ ሸክም ነው፤ መራመድም ተስኖአቸዋል››

የክፉ አድራጊ ዘር

‹‹ዘር›› የሚለው ቃል ሌሎች ያደረጉትን የሚያደርጉ ሰዎች መጠሪያ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሌሎች ያደረጉን ክፉ ነገር የሚያደርጉ ሰዎች››

በደል ፈጸሙ

ክፉ አደረጉ

ያህዌን ተዉ

‹‹ከያህዌ ራቁ››

እርሱን ናቁ

‹‹መታዘዝ አልፈለጉም›› ወይም፣ ‹‹እርሱን አላከበሩም››

እስራኤል

ይሁዳም የእስራኤል ሕዝብ አካል ነበር፡፡

ጀርባቸውን በእርሱ ላይ አዞሩ

ምንም እንኳ በአንድ ወቅት ወዳጆቹ የነበሩ ቢሆንም፣ አሁን ግን ጨርሰ እንደማያውቁት ሆኑበት፡፡