am_tn/isa/01/02.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ በግጥም መልክ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

ሰማያት ሆይ ስሙ፤ ምድርም አድምጪ

ምንም እንኳ እነዚህ ትንቢቶች የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ሕዝብ እንዲሰሙ የተነገሩ ቢሆኑም፣ ኢሳይያስ እንደማይሰሙ ያውቃል፡፡ ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ሰማያት›› እና ‹‹ምድር›› ያህዌ የተናገረውን መስማት እንደሚችሉ በሚያመለክት ሁኔታ መናገሩ ነበር፤ ወይም 2) ‹‹ሰማያት›› እና ‹‹ምድር›› በየአገሩ ሁሉ ያሉ ሰብዓዊ ፍጡራን ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሰማያት የምትኖሩ… በምድርም የምትኖሩ››

ያህዌ

ይህ በብሉይ ኪዳን ዘመን ለነበሩ ሕዝብ የተገለጠ የእግዚአብሔር ስም ነው፡፡ ይህን እንዴት እንደምትተረጒም በትርጒም ገጽ ስለ ያህዌ የተነገረውን ተመልከት፡፡

መገብኃቸው እነርሱ ግን አላወቁም

ያህዌ ለሕዝቡ የተናገረውና ኢሳይያስ በያህዌ ምትክ ለእስራኤል የተናገረው ቃል

ልጆች ወለድሁ አሳደግኃቸውም

የእርሱ ቃል ምግብ፣ እስራኤላውያን ደግሞ ልጆቹ እንደ ሆኑ ያህዌ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በይሁዳ ለሚኖሩ ሰዎች እንደ ልጆቼ ተጠነቀቅሁ››

አህያ የባለቤቱን ጋጥ

በውስጠ ታዋቂነት የተቀመጠውን መረጃ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አህያ የሚመገብበትን የጌታውን ጋጥ አወቀ›› ወይም፣ ‹‹አህያ ጌታው ለእርሱ ምግብ የሚሰጥበትን አወቀ››

እስራኤል ግን አላወቀም፤ እስራኤል አልተረዳም

ይህም ማለት፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ ግን አላወቁኝም፤ ለእነርሱ የምጠነቀቅ መሆኔን አልተረዱም››

እስራኤል

ይህ የእስራኤል ሕዝብ መጠሪያ ነው፡፡ ይሁዳም የእስራኤል ሕዝብ አካል ነበረ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ››