am_tn/isa/01/01.md

1.2 KiB

ኢሳይያስ ያየው ራእይ

‹‹ይህ ያህዌ ያሳየው የኢሳይያስ ራእይ ነው›› ወይም፣ ‹‹ይህ ያህዌ ለኢሳይያስ ያሳየው ነው››

አሞጽ

አሞጽ የኢሳይያስ አባት ነው፡፡

ይሁዳና ኢየሩሳሌም

‹‹ይሁዳ›› ደቡባዊው የእስራኤል መንግሥት ነው፡፡ ‹‹ኢየሩሳሌም›› በጣም አስፈላጊ ከተማ ናት፡፡ የቦታዎች ስም በውስጣቸው የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ›› ወይም፣ ‹‹የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች››

በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን

ይህ እያንዳንዱ ንጉሥ የገዛበትን ዘመን ያመለክታል፡፡ የገዙት ተራ በተራ እንጂ፣ ሁሉም በአንድ ጊዜ አልነበረም፡፡ አማረጭ ትርጒም፣ ‹‹ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝና ሕዝቅያስ የይሁዳ ነገሥታት በነበሩ ጊዜ››