am_tn/hos/14/04.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው እኔ መሸሻቸውን እፈውሳለሁ/አስቀራሉ ህዝቡ ከእግዚአብሔር መሸሹን ማስቆም የተገለጸው እርሱ እንደሚፈውሳቸው ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእነርሱ ፊታቸውን ማዞር

የህዝቡ እግዚአብሔርን አለመታዘዝ የተገለጸው በአካል ከእርሱ ፊታቸውን እንዳዞሩ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ለእስራኤል እንደ ጤዛ እሆናሉ፤ እርሱም ውብ አበባ ይሆናል፡፡

እግዚአብሔር እዚህ ስፍራ የተገለጸው ለተክሎች ተፈላጊውን እርጠበት እንደሚሰጥ ጤዛ ሲሆን፣ እስራኤል አንድ ሰው እንደሆነና እንደሚፈካ አበባ ሆኖ ቀርቧል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

እንደ ሊባኖስ ዝግባ ስር ይሰዳል

እዚህም ስፍራ እንደ ተክል የቀረበው የእስራኤል ስዕል ቀጥሏል፣ በዚህ ጊዜ ግን እስራኤል ሊባኖስ እንደምትታወቅበት እንደ ረጅም የዝግባ ዛፍ ቀርቧል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በሊባኖስ እንደሚገኝ ዝግባ … ስሮቹ ይዘረጋሉ

ምንባቡ በተመሳሳይ ምስል ይቀጥላል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)