am_tn/hos/13/15.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ነቢዩ ሆሴዕ እየተናገረ ነው

ወንድሞቹ

ይህ አገላለጽ በሰሜን መንግሥት ዙሪያ ለሚገኙ አገራት፣ በተለይ የደቡብ መንግሥት ለሆነው ለይሁዳ የቆመ ይመስላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የምስራቅ ነፋስ፣ የያህዌ ነፋስ ይመጣል

ከምስራቅ የሚመጣ ነፋስ በጣም ሞቃት እና አጥፊ ነበር፡፡ እዚህ ስፍራ ያህዌ የእስራኤልን ሰዎች እንዲየጠፉ ከምስራቅ የሚልካቸውን ወታደሮች ያመለክታል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የኤፍሬም ምንጮች ይደርቃሉ፣ ጉድጓዶቹም ውሃ አይኖራቸውም

ሆሴዕ እግዚአብሔር እንዴት የእስራኤልን ሰዎች እንደሚቀጣ መግለጹን ይቀጥላል፡፡ እዚህ ስፍራ ውሃ ህይወትን፣ ጥንካሬን እና ብርታትን ይወከወላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ግምጃ ቤት

ይህ ሁሉንም የህዝቦች ሃብት ያመለክታል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)