am_tn/hos/13/14.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

ከሲኦል እጅ አድናቸዋለሁን? ከሞት እታደጋቸዋለሁን?

ያህዌ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመባቸው ለእስራኤል ህዝብ ከመሞት እንደማያድናቸው ሊነግራቸው ነው፡፡ በእርግጥ ይቀጣቸዋል፡፡ "በእርግጥ ከሞትና ወደ ሲኦል ከመውረድ አላድናቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሞት ሆይ መቅሰፍትህ የት አለ? ሲኦል ሆይ ጥፋትህ ወዴት አለ?

ሰዎች የሆኑ ያህል፣ ያህዌ ለ"ሞት" እና "ሲኦል" እየተናገረ ነው፡፡ ያህዌ ጥያቄዎቹን የተጠቀመባቸው ሰዎቹን በቶሎ እንደሚያጠፋቸው ለመናገር ነው፡፡ "የእስራኤል ሰዎች እንዲሞቱ አሁን መቅሰፍትን አደርጋለሁ፡፡ አጠፋቸዋለሁ ደግሞም ወደ ሲኦል እልካቸዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ፣ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከዐይኖቼ ርህራሄ ተሰውሯል

ርህራሄ እንዳለ እንዳያስቡ ርህራሄ እንደሚደበቅ ነገር ተደረጓ ተገልጽዋል፣ ስለዚህም ሊታይ አይችልም፡፡ ረቂቅ ስም የሆነው "ርህራሄ" ከገላጭ ጋር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እኔ ለእነርሱ ርህራሄ የለኝም" ወይም "እኔ ለእነርሱ ርህሩህ አልሆንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)