am_tn/hos/13/12.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

የኤፍሬም በደል ተከማችቷል፣ ኀጢአቱም ሞልቷል

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ናቸው፤ትረጉማቸውም በመሰረታዊነት አንድ አይነት ነገር ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ)

ሞልቷል/ተከማችቷል

የሰሜኑ መንግት ሀጢአት እና በደል ለጉዳይ ሊጠበቅ እንደሚችል ቁሳዊ አካል እንደሆኑ ተደርጎ ቀርቧል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ልጅ የመውለድ ምጥ አይነት ስቃይ በእርሱ ላይ ይመጣል

እዚህ ስፍራ ያህዌ የእስራኤል ህዝብ ሊደርስበት ያለውን መከራ ልጅ ሲወለድ ሴት ያለባትን የምጥ ስቃይ ያህል እንደሆነ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን እርሱ ብልህ ያልሆነ ልጅ ነው፣ የመወለድ ሰአት በደረሰ ጊዜ፣ ከማህጸን አይወጣም

አሁን ያህዌ የእስራኤልን ህዝብ የሚገልጸው እናት እንደምትወልደው ህጻን ነው፡፡ ህጻኑ ብልህ አይደለም ምክንያቱም ለመወለድ አልፈለገም፡፡ ህዝቡ ንስሃ ሊገባ እና ያህዌን ሊታዘዝ አልፈለገም፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)