am_tn/hos/13/01.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

ፍሬም ሲናገር

ሆሴዕ "ኤፍሬም" የሚለውን ቃል የተጠቀመው፣ ምንም እንኳን ከአስሩ ነገዶች የአንዱ ስም የነበረ ቢሆንም፣ መላውን የሰሜን መንግሥት ለማመልከት ነው፡፡ ሆሴዕ እንደ አሁኑ ጊዜ ሳይሆን የሰሜኑ መንግሥት ጠንካራ እና የተከበረ ስለነበረበት ስለ ቆየ የጥንት ዘመን የሚናገር ይመስላል፡፡ (ስኔቲክ/ዘይቤያዊ አነጋገር- የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውም ይመልከቱ)

መንቀጥቀጥ ነበር

ህዝቡ ይንቀጠቀጥ እንደነበር ይታወቃል ምክንያቱም ኤፍሬምን ይፈሩት ነበር፡፡ ይህ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በህዝቡ መሃል መንቀጥቀጥ ነበር" ወይም "ሰዎች በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ራሱን በእስራኤል አላቀ

እዚህ ስፍራ "አላቀ" ማለት ራስን ጠቃሚ አድርጎ ማሳየት ማለት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን በዓልን በማምለክ ኀጢአተኛ ሆኖ ተገኘ፣ ሞተም

የኤፍሬም ሰዎች በዓልን ምማለክ ሲጀምሩ፣ ደካሞች እየሆኑ ይመጣሉ፤ ጠላቶቻቸውም ያሸንፏቸዋል፡፡ እዚህ ስፍራ "ሞተ" የሚለው የሚያመለክተው አገሪቱ እየደከመች መምጣቷን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አሁን በደላቸው እየጨመረ ሄደ

እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው የሚያመለክተው የኤፍሬምን ምሳሌነት የተከተሉትን የኤፍሬምን ነገድ እና መላውን የእስረኤል አገር ነው

እነዚህ ለጣኦት መስዋዕት የሚያቀርቡ ሰዎች ጥጃዎቹን ይስማሉ

የጣኦት አምልኮ አንዱ ክፍል የተቀረጸውን የጥጃ ጣኦት ምስል መሳም ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)