am_tn/hos/11/08.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ስለእስራኤል እየተናገረ ነው

ኤፍሬም ሆይ፣ እንዴት ልተውህ እችላለሁ? እስራኤል ሆይ፣ እንዴት አሳልፌ ልሰጥሽ እችላለሁ?

ያህዌ ህዝቡን እጅግ ስለሚወድ ሙሉ ለሙሉ አያጠፋውም፡፡ ይህ ከጥያቄ መልክ ወጥቶ በዐረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ኤፍሬም ሆይ፣ እኔ አልተውህም፡፡ እስራኤል ሆይ፣ እኔ አልጥልሽም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዩ አድግሃለሁ?

ያህዌ ህዝቡን እጅግ ስለሚወድ ሙሉ ለሙሉ አያጠፋውም፡፡ ይህ ከጥያቄ መልክ ወጥቶ በዐረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በአዳማ ላይ እንዳደረግኩት በአንተ ላይ ማድረግ አልገልግም ወይም በሶዶም ላይና በሲባዩ ከተሞች ላይ እንዳደረግኩት አላደርግብህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

እኔ እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለሁም

እግዚአብሔር በፍጥነት ለመበቀል እንደሚወስኑት እንደ ሰዎች አይደለም

ልቤ በውስጤ ተለወጠ

እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚለው የሚወክለው የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና ውሳኔ ነው (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለው ይመልከቱ)

በቁጣ አልመጣም

"ቁጣ" የሚለው ረቂቅ ስም "ቁጡ" በሚለው ገላጭ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ወደ እናንተ መጥቼ በእናንተ ቁጡ አልሆንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)