am_tn/hos/11/01.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ፣ ወላጅ ልጁን እንደሚንከባከብ፤ እስራኤልን ስለመንከባከብ ይናገርል

እስራኤል ወጣት ሰው በነበረበት ወቅት

ያህዌ ስለ እስራኤል ሰዎች ወጣት ሰው እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ ያህዌ ከአገሪቱ ጋር በመጀመሪያ ግንኙነት ሲጀምር የነበረውን ሁኔታ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ልጄን ከግብጽ ጠራሁት

"ወንድ ልጅ" የሚለው የሚያመለክተው የእግዚአብሔር አብን ህዝብ ነው፡፡ "ልጄን ከግብጽ አወጣሁት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አብዝተው በተጠሩ መጠን፣ አብዝተው ከእርሱ ራቁ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የእኔ ህዝብ እንዲሆኑ አብዝቼ በጠራኋቸው መጠን፣ አብዝተው ተቃወሙኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)