am_tn/hos/10/12.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

ጽድቅን ለራስህ ዝራ፣ የቃል ኪዳንን ፍሬ በታማኝነት እጨድ

ጽድቅ እና የቃል ኪዳን ታማኝነት የተነገሩት እንደሚዘራ እና እንደሚታጨድ እህል ነው፡፡ ረቂቅ ስም የሆኑት "ጽድቅ" እና "ታማኝነት"፤ "ትክክል" እና "ታማኝ" ተብለው ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "አሁን እረስ፣ ደግሞም ትክክል የሆነውን አድርግ፤ ይህ ሲሆን የታማኝነትን ፍቅር ፍሬ ማጨድ ትችላለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

ያልታረሰ መሬታችሁን እረሱ

መሬት "ሳይታረስ ሲቀር" በላዩ ለመዝራት ዝግጁ አልተረገም ማለት ነው፡፡ ያህዌ ህዝቡ ንስሃ እንዲገባ እፈልጋለሁ ማለቱ ነው፤ ስለዚህ ትክክል የሆነውን ማድረግ መጀመር ይችላሉ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኀጢአትን አርሳቸርኋል፤ ኢፍትሃዊነትን አጭዳችኋል

ኀጢአት እና ኢፍትሃዊነት የተገለጹት ሊዘራ እና ሊታጨድ የሚችል ሰብል እንደሆኑ ተደርጎ ነው (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የማታለልን ፍሬ ተመግባችኋል

የማታለል ውጤቱ የተገለጸው ሊበላ እንደሚችል ምግብ ነው፡፡ "አሁን አንዳችሁ ሌላችሁን ማታለላችሁ የሚያስከትለውን የመከራ ውጤት እየተቀበላችሁ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)